ከቀዳማዊ ኃይለሥላሤ ባሕር ኃይል እስከ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ልዩ ልዩ ፎቶግራፎች። የብሪታኒያ ባሕር ኃይል አባላት ምፅዋ ባሕር ኃይል መደብ በተገኙ ጊዜ የነበሩ አጋጣሚዎች ነው አንዳንዶቹ ፦ THE ROYAL ETHIOPIAN NAVY , SOCIALIST ETHIOPIAN NAVY ( After Emperor Haileslassie Deposed by Military Coup ) PICTURES & ALSO THE ROYAL GREAT BRITAIN NAVY OFFICERS IN ETHIOPIA AT MASSAWA SEA PORT ON THE OCCASION OF NAVY DAY ( IN 1960S) . -- ETHIOPIAN NAVY WAS ESTABLISHED BY NORWEGIAN NAVY ; THEN THE ROYAL GB NAVY HAD SECONDED ETHIOPIAN PERSONNEL TO ITS BASES IN ERITREA TO PROVIDE THEM WITH NAVAL TRAINING. THE NAVAL COLLEGE , WHERE ETHIOPIAN NAVAL OFFICERS UNDERTOOK A 52 MONTH PROGRAM STUDY WAS FOUNDED AT ASMARA IN 1956.
Ethiopian Navy Day In 1987 GC የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ቀን 1979ዓም
ETHIOPIAN NAVY DRILL TEAM IN 1987 GC ( 1979 Ethiopian Calendar )
ETHIOPIAN NAVY PARADE 1987 EC (Massawa Naval Base)
የ 1975 Intake የባሕር ኃይል አባላት ፕሬዚደንት መንግሥቱ ኃ/ማ የባሕር ኃይላችን ቀንና ዕጩ መኮንናትን ለመመረቅ በተገኙበት የዘመሩት የባሕር ኃይላችን ቃልኪዳን መዝሙር
TEDDY AFRO'S SONG IN ENGLISH ' MOTHERLAND '
ETHIOPIAN ARMY MARCHING BAND PLAYS UK NATIONAL ANTHEM
የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል መኮንኖች ፎቶግራፎችና ፤ ዕጩ መኮንኖችን ቀዳማዊ ኃይለሥላሴና ፤ ፕሬዚዳንት መንግስቱ ኃ/ማርያም ሲመርቁና የክብር ዘቡን ሲጎብኙ...…
VARIOUS PICTURES OF THE FORMER ETHIOPIAN NAVY SENIOR COMMANDING OFFICERS VISITING ABROAD INCLUDING OUR COUNTRY ETHIOPIA PREVIOUS LEADERS
ETHIOPIAN NAVY DAY MEMORIAL IN 2018 ADDIS ABEBA የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አባት ጦር አባላት ' የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ቀን ' ትዝታ ከ LTV ጋር በመተባበር አዲሱን አመት 2011 ን በደማቅ ስሜት አክብረዋል
በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው የረጅም ርቀት የሚሳይል ተኩስ ሙከራ የተደረገው በኢትዮጵያ ባህር ሃይል ፈጣን አጥቂ 111ኛ ስኳድሮን ከነበሩት አንዷ በ FMB-163 ጦር መርከብ ነበር
ETHIOPIAN NAVY HEROES HONOURED IN WASHINGTON DC - በዚህ ቪዲዮ የጀግኖች ምሽት ላይ በ 20 ኪ.ሜ ምሽግ ተሠራ የሚባለው በ 20 ኪሜ የ Firing Zone ወይም በ 20ኪሜ ከመደቡ ርቀት አቅጣጫ የቤኤም-21 የተኩስ ልምምድ ተደረገ ተብሎ ይታረምልን ? ስህተት ነው
ከዌብሳይቱ ጀርባ የሚታየው ፎቶግራፍ ፈረንጆች ቀይ ባሕር ጥልቀት ላይ ( SEA BED) ገብተው በ UNDER WATER CAMERA ያነሱት ፎቶግራፍ ነው
IF YOU WOULD LIKE TO SHARE THE WEBSITE TO OTHERS, PLEASE CLICK THE FACEBOOK ICON.
ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ዌብሳይቱ እንዲታይ ከፈለጉ በስተቀኝ ያለውን የ FACEBOOK አርማ ይጫኑ
IF YOU WOULD LIKE TO SHARE THE WEBSITE TO OTHERS, PLEASE CLICK THE FACEBOOK ICON.
ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ዌብሳይቱ እንዲታይ ከፈለጉ በስተቀኝ ያለውን የ FACEBOOK አርማ ይጫኑ
የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል መታሰቢያ ዓላማ የአገልግሎት ዘመን ትዝታችንን በማስታወስ ኢትዮጵያ ሃገራችን ባለባሕር በር ሃገር መሆኗን፤ ኢትዮጵያዊ መጪው ትውልድም ይሁን አሁንም ' ሕ ወ ሃ ት ' ወያኔ በሚዲያው አደንዝዞ ግራ ያጋባውን ሕብረተሰብ የአሰብ ወደብ ባለቤትነቱን እንዳይረሳና ወያኔ ከተወገደ በኋላ መብቱን እንዲያስከብር ማስታወሻ ነው።
እንደሚታወቀው የባሕር ኃይላችን ቀይ ባሕራችንን በማስከበር ረገድ አንድም ጊዜ በውጭ ወራሪ ኃይል ያለመደፈራችን ምክንያት የባሕር ኃይላችን ብቃት ከአካባቢው ሃገራት የተሻልን በመሆናችን በገሃድ የሚታወቅ ሃቅ ነበር። እንኳንስ አሁን ወንበዴዎች ሃገሪቷን የባሕር በሯን በዘጉበት ዘመን ይቅርና በደርግ የኢትዮጵያ መንግሥት ዘመን የባሕር ኃይላችን ሚና በቂ የሚዲያ አገልግሎት ጊዜ ተሰጥቶት ሕዝባችን ምን እያደረግን እንደነበርን የሚያውቀው ነገር አልነበረም። የምድር ጦርና የአየር ኃይል አባላትም ቢሆኑ ስለ ባሕር ኃይላችን ቀይ ባሕርን በማስከበሩ ረገድ የሚያደርገውን ትሩፋት በአጋጣሚ ከአሰብ ምጽዋ ወይም ወደ ሰሜኑ የጦር ግምባር የባሕር ጠረፍ በሚደረገው ጉዞ ሁኔታ ካላዩ በስተቀር ብዙም የሚያውቁት ጉዳይ አልበረም። ኢትዮጵያ በ 36ቱ የዘመናዊው የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አገልግሎት ዘመን በውጭ ወራሪ ኃይል ተደፍራ አታውቅም። ሻቢያ በውጭ ሃገራት ተደጋግፎ በሌለው አቅም ሥልጣን ከያዘ በኋላ የነዳጅ ክምችት አላቸው የሚባሉትን ' የሃኒሽ ደሴቶችን ' በየመን ተሸንፎ ሲያስረክብ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አባል ቁጭቱንና እልሁን ሆድ ይፍጀው ብሎ ዝም አላለም። ኤርትራ ራሷን ችላ የምትገነጠል ከሆነ '" ደንከል አውራጃና አሰብ ወደብን ጨምሮ ባለቤቱ ቀደም ብሎም በወሎ ክፍለሃገር አውሳ አውራጃ '" በደርግም ዘመን ደንከል አውራጃ '" አሰብ ራዝ ገዝ ''' ሆኖ ራሱን የሚያስተዳድር ክልል ነበር። መፃኢው ተመራጭ መንግሥት የኢትዮጵያን ሕልውና ለማረጋገጥ ቆራጥ ሆኖ የጥንቱም ማስረጃ በተባበሩት መንግሥታት ጽ/ ቤት አለና በሰላማዊ መንገድ የማስከበር ታላቅ የታሪክ አደራ ኃላፊነት አለበት። ድኅነታችን በገዛ ወደባችን የወደብ ቅኝ ተገዢ መሆናችን የኢኮኖሚ ምሁራን ይናገራሉ ፤ ፪ቱም ወደቦቻችን በእኛ ቁጥጥር ሥር በነበሩ ዘመን ግለሰብም ይሁን የመንግሥት ፋብሪካዎችና ልዩ ልዩ ተቋማት ከውጭ ሃገር ለሚያስገቡት ሸቀጥና ንብረት ለወደቦቹ የሚከፍሉት በውጭ ምንዛሪ ' በዶላር ' ሳይሆን በራሳችን " በብር " ነበርና ብራችንም በዓለም ሃገራት ኃይልና ዋጋም ነበረው። ያለባሕር በር ሕ ወ ሃ ት ለሠራው የብሔር ፌዴራሊዝም ለክልል ግንጠላ የምትታገሉ የዘመኑ እንቆቅልሾች ሕልማችሁ እውን ቢሆን የወደብ ባርነቱ ቀንበር ይብስባችኋል። ኢትዮጵያዊነት አንድነትና ኅይል ነው ፤
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
አሜን።
የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አባላት "በሕይወት ያሉና "፡ እናት ዓለም ኢትዮጵያን የባሕር ድንበሯን ሲጠብቁ ና ሲያስከብሩ የወደቁ አባሎች ፎቶግራፎች. THE FORMER ETHIOPIAN NAVY RATING MAMBERS ALIVE & FALLEN ON LINE OF DUTY DUE TO THE MOTHERLAND ETHIOPIA TERRITORIAL INTEGRITY
PAUSE የሚለውን ቃል በመጫን አቁመው መመልከት ይችላሉ
10 COMMANDMENTS OF THE ETHIOPIAN NAVY DAMAGE CONTROL WAS
1- KEEP YOUR SHIP WATER TIGHT
2- DO NOT VIOLATE MATERIAL CONDITION
3- HAVE CONFIDENCE IN YOUR SHIPS ABILITY TO WITHSTAND DAMAGE
4- KNOW YOUR WAY AROUND- EVEN IN THE DARK
5- KNOW HOW TO USE AND MAINTAIN DAMAGE CONTROL EQUIPMENT
6- REPORT DAMAGE TO NEAREST DAMAGE CONTROL REPAIR STATION
7- KEEP PERSONAL ARTICLES PROPERLY SECURED
8- PRACTICE PERSONAL DAMAGE CONTROL; PROTECT YOURSELF SO YOU CAN PROTECT YOUR SHIP
9- TAKE EVERY POSSIBLE STEP TO SAVE THE SHIP AS LONG AS A BIT OF HOPE REMAINS
10- KEEP COOL, DON'T GIVE UP THE SHIP
ከሕንድ የባሕር ኃይል ጦር መርከብ ሚዚየም ላይ ግለሰብ በሞባይል ቴሌፎን ቀርጾ ፌስቡክ ላይ ጭኖት ያገኘሁት ሲሆን ሁሉም ነገሯ አንድ ዓይነት OSA CLASS MISSILE LOUNCHING የጦር መርከብ ስለሆነች ለእኛም ትዝታ፦
ኤርትራ ከተገነጠለች አሰብ ወደብም ሆነ ደንከል አውራጃ ከደቡብ ቀይ ባሕር ጋር ቀሪነቱ የኢትዮጵያ ነው
ክቡር ዶክተር አምባሳደር ካሣ ከበደ፡ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አባላት፡ በየመን ሃገር ለ 11 ዓመታት ሲንገላቱ በቆዩበት ዘመን በተቻላቸው መጠን ሁሉ ታግለው እያንዳንዱ የባሕር ኃይል እስከነቤተሰቡ ወደ አሜሪካን ሃገር እንዲዛወሩ ሃሳባቸውና ጥረታቸው ተሳክቶላቸዋል። በርግጥም ክቡር ኮማንደር አሠፋ ሠይፉም የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት ማድረጋቸው ከእያንዳንዱ የባሕር ኃይል ታላቅ ምሥጋና ያቀርባሉ። ክቡር ዶክተር አምባሳደር ካሳ ከበደ፤ ክቡር ኮማንደር አሠፋ ሠይፉ፤ እንዲሁም በዚህ የተቀደሰ ተግባር የተቻላችሁን ጥረት ያደረጋችሁ ሁሉ፡ ፈጣሪ የኢትዮጵያችን አምላክ ረጅም ዕድሜና ጤና እንዲሰጥልን ፀሎታችን ነው። ክቡር አምባሣደር ካሣ ከበደ በሞት ቢለዩንም እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማርልን፡፤