ሪር አድሚራል ተስፋዬ ብርሃኑ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ዋና አዛዥ ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያም ከምፅዋ ወደ አሰብ በተጓዙ ወቅት ስለቀይ ባሕር በጦር መርከብ ኢትዮጵያ ላይ ሆነው ገለጻ ሲያደርጉ
![]() የጀግናው ዘርዓይ ደረስ እናት በጀግናው ልጃቸው በተሰየመችው የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጦር መርከብ ላይ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት( እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1950ዎቹ ዓም ![]() ራስ አሉላ (አባ ነጋ) የደርቦሾችን ( የግብጾችን) መሪ ፓሻውን በጦርነቱ ላይ ከገደሉ በኋላ የፓሻውን ዩኒፎርም ለብሰው ለማስታወሻ የተነሱት ፎቶግራፍ ነው የራስ አሉላ እንግዳ( አባ ነጋ) የዶጋሊ ጀግንነት ተጋድሎ በአውሮፓ ዜናው እንደተሰማ ጎብኚዎች እርሳቸውን ለማየት በዚያን ዘመን አጠራር ሃማሴን አሁን አሥመራ ድረስ ይመጡ ነበርና፡ አንድ አውሮፓዊ ፡ አሥመራ እንደደረሰ ለራስ አሉላ ልዩ ስጦታ ይዤ መጥቻለሁና እባካችሁ አቅርቡኝ ብሎ በጠየቀው መሠረት ከአስተርጓሚ ጋር ይቀርባል። ራስ አሉላ ቁመታቸው አጭር ስለነበር ጎብኚው እፊታቸው ቀርቦ ግራ ተጋባ፡ ለአስተርጓሚው እኔ የመጣሁት ራስ አሉላን ለማየትና ስጦታ ላበረክት ነውና እባክህ የታሉ በማለት ጠየቀ፡ እኚህ ናቸውኮ ብሎ አስተርጓሚው ሲነግረው አላመነም። እኔኮ ራስ አሉላ ማለት ግዙፍ ሰው ነበረ የምጠብቀው ብሎ ተናገረ። አስተርጓሚው ሁኔታውን ተርጉሞ ለራስ አሉላ እንደነገራቸው ወዲያውኑ ፡ ንገረው!!! ግማሹ ሰውነቴ መሬት ውስጥ ነው ያለው ብለው ተናገሩ፤ ጎብኚውም ስጦታውን ሲያበረክት ፡ ተከፍቶ ሲታይ አዲስ ጠመንጃ ነበር። ራስ አሉላም በጦርነት ከማረኩት ልዩ ጠመንጃዎች አንዱን ሸልመው ብልህነታቸውን በጥበብ ነግረው በጥበብ ሸልመው አሰናብተውት እንደነበር ቀደም ካሉ መጻሕፍት አንብበናል። ![]() ስለ የኢትዮጵያ ጀግናው የሃማሴን ተወላጁ ዘርዓይ ደረስ ታሪክ ሲነገር በሻቢያ ዘመን ኤርትራ ውስጥ ለነበሩ ወጣቶች እንግዳ ነገር ነው። ምክንያቱም ሻቢያ ገና ከጀብሃ ከሚባሉት የአረብ ፈላሻዎች ተገንጥሎ ከመውጣቱ አስቀድሞ ምሥረታው በጣሊያን ባንዳ አሽከሮች (ሹምባሽ) በነእድሪስ አወቴ ሱዳን ውስጥ በሶርያውያን ረዳትነት ሲመሠረት ፀረ ኢትዮጵያዊነት እነደነበር አያውቁምና። ሻቢያ ለኤርትራ ሕዝብ ልክ እንደወያኔ አዳዲስ የወሬ ፈጠራ ታሪክ በመመሥረት ኢትዮጵያዊ ስሜት እንዳይኖራቸው አዳዲሱን ትውልድ ቅኝ፡ገዢዎቻቸው በባርነት በሰጧቸው ስም የታሪክ ክህደት የተነሳ፡ የዚያን አካባቢ የጥንት ስም ማለትም " ባሕረ ነጋሲ ወይም ባሕረ ነጋሽ " የሚለው ስም እንዲጠፋ አድርገዋል። ስለራስ አሉላ እንዳይነሳ ደርግ የፈጠረው እንጂ በታሪክ ራስ አሉላ የሚባል ነገር የለም በማለት ናፅነት እንዳሉት ሳይሆን አዲስ ለፈጠሩት ስደተኛ ትውልድ አስተምረዋል። ስለዘርዓይ ደረስ ሲነሳ አንድ ግለሰብ በማለት አጥላልተዋል። ዘርአይ ደረስ ግን ባርነት የማይስማማው ኢትዮጵያዊ ሆኖ በጠላት የሙሶሊኒ ኢጣሊያን ወታደር ሶላዳቶዎች በረገጧት ሰንደቅ ዓላማችን ውርደት እነደነሻቢያ-ወያኔዎች ሳይክድ፡ ስለሃገሩ ኢትዮጵያ ፍቅር ማድረግ የሚገባውን በጀግንነት ተወጥቷል። ኢትዮጵያ ሃገራችን በግርማዊ ጃንሆይ ዘመነ አጼ ዮሓንስ 4ኛ ስትስተዳደር ፡ ቅኝ ገዢዎች እንዲሁም ደርቡሾች( ግብጾች ) የአባይ ወንዝ መነሻ የሚያጠቃልል ካርታ ለመመሥረት ቋምጠው ተደጋጋሚ ጥቃት ቢያደርሱም በፍጹም አልተሳካላቸውም ነበር። በኤርትራ አካባቢ ያለውን መላ ክልል እንዲያስተዳደሩ የተሾሙት ራስ አሉላ አባ ነጋ ተደጋጋሚ የደርቡሾችን ( የግብጾችን ) ጥቃት በተለይም በጉራዕና በጉንዳጉዲ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ 1875 እስከ 1876 የግብጹን የጦር መሪ ( ፓሻ) ማርከውና ገድለው ለመታሰቢያ የፓሻውን ዩኒፎርም ለበሰው ፎቶግራፍም ተነስተዋል። በከረንና ኩልፊት እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1885 የግብጽ ማህዲስቶች ወይም ደርቡሾችን ድል አድርገዋል። ከማሕዲስቶች ጋር ጦርነት ገጥመው በማካሄድ ላይ እያሉ ጣሊያኖች ምፅዋን ተቆጣጥረው ስለነበር፡ ጦርነቱን በድል አጠናቀው ሳለ ፊታቸውን ወደ ምፅዋ ባዞሩ ዘመን፡እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1887 ዓም ጣሊያኖች ጭራሽ መላውን ኤርትራ ለመያዝ ከምጽዋ ተነስተው ሲገስግሱ ራስ አሉላ ዶጋሊ ላይ የጣሊያን ጦር ሲደርስ ድንገተኛ ማጥቃት ሰንዝረው ከ500 በላይ ጣሊያኖችን በመማረክና በመግደል የድሉ ባለቤት እንደነበሩ፡ የኢትዮጵያ ታሪክ መዛግብት ላይ በተደጋጋሚ ተጽፏል። በኋላም ደርቡሾች መተማ ላይ ኃይለኛ ጦርነት በከፈቱበት ወቅት እራሳቸው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት አጼ ዮሕንስ ዘምተው በጦርነቱ ላይ ተሰውተዋል። አጼ ዮሓንስ ከአረፉ በኋላ፡ የኢትዮጵያ ጦር ኃይል የመሪው መሞት በድንጋጤ በመዳከሙ፡ የጣሊያን ጦር መላውን ኤርትራ በመቆጣጠር የጣሊያን መንግሥት ቅኝ መሬት አደረገው። ጣሊያኖች በእምዬ ምኒልክ በ1896 ዓም አድዋ ላይ በተሸነፉ በ40ኛው ዓመት እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1928 ዓም መላውን ኢትዮጵያ ወረሩ ፡ ከዚያም በዘረፋ የራሳቸው ታሪክ ያልሆኑትን የሃውልት ሌብነት ሲያደርጉ ከአክሱም አንድ ሃውልትና፡ ለገሃር የነበረውን የይሁዳ አንበሳ ሃውልት ነቅለው ጣሊያን ዋና ከተማ " ሮማ " ላይ ተከሉት። ከዕለታት በአንዱ የጣሊያን አመታዊ በዓላቸው ቀን ፡ ጀግናው ዘርዓይ ደረስን ከአሥመራ በጣሊያን ቋንቋ አስተርጓሚነት ወስደውት እዚያው ስለነበር፡ የሃገሩን የአርበኝነት ዩኒፎርም እስከነ ሙሉ ትጥቁ ጎራዴውን ጨምሮ ለብሶ በዓሉ ቦታ ላይ እንዲገኝ አደረጉ። ከዚያም የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን መሬት ላይ አንጥፈው እየረገጡና ምራቃቸውን እየተፉ ሲረማመዱበት ጀግናው ወጣቱ ዘርዓይ ደረስ መታገስ አልቻለም፤ አጠገቡ ካሉት በመጀመር የጣሊያን ወታደሮች አንገት መቀንጠስ ጀመረ፤ ጣሊያኖች እግሬ አውጪኝ ሽሽት ጀመሩ፡ ዘርዓይ ደረስን የሚያስቆመው የሰው ክንድ እንዳልሆነ አወቁ፡ ወዲያው ተኩሰው እግሩን አቆሰሉት። ወደ እስር ቤት አስገብተውት ቢሆንም ጀግንነቱ በመላው ጣሊያን ሃገር ገነነ። ሆስፒታል አስገብተው በሕክምና ሂደት ላይ ሳለ፡ ኢትዮጵያ ሃገራችን ድል እንደተቀዳጀች፡ ሙሶሊኒ በገዛ ሕዝቡ ተገድሎ አዲስ የጣሊያን መንግሥት ስለተመሠረተ፡ ግርማዊ ጃንሆይ አጼ ኃይለሥላሤ፡ በምርኮና በግዞት ጣሊያን የወሰዳቸውን አርበኞች ሲያስመልሱ፡ ጣሊያኖች ሆን ብለው ይህንን ወጣት ጀግና ገድለው ታሞ ሞተ በማለት ሕይወቱን ቀጥፈውት እንደነበር የኢትዮጵያ ታሪክ ጻሕፍትና የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት መምሕራኖች በተደጋጋሚ በመዘከር የዘርዓይ ደርስን ትሩፋት ነግረውናል፤ አስተምረውናል። የጀግንነት ስሙ ለዘለአለም ሲታወስ ይኖራል፡፤ ![]() ይሕች የጦር መርከብ በዘመነ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃያለሥላሤ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተገዝታ በጀግናው ዘርዓይ ደረስ ስም ተሰይማ የነበረች የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የጦር መርከብ ናት። ![]()
|