እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አባል የነበረ መኮንንም ይሁን የበታች ሹም የኢትዮጵያ ባሕር ኃይላችንን ትዝታ በተመለከተ ሁሉም የራሱ PERCEPTION ይኖረዋልና በዚህ የባሕር ኃይላችን መታሰቢያ ዌብሳይት የሚሰማኝን ለሕዝብ በንባብና ከየአባሎቻችን ያገኘኋቸውን ፎቶግራፎች በመለጣጠፍ ለማሳየትና ለማስነበብ እየጣርኩ ነው። ክቡር ኮማንደር ታመነ ጃለታን በቅርብ ባላውቃቸውም በየጊዜው ወሳኝ ለሆኑ ከሌሎች የጦር ኃይሎች ማለትም ከምድር ጦርና ከአየር ኃይል ጋር በሕብረት ለሚደረግ ዘመቻዎች የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ እውቀታቸውን በሥራ እንዲያውሉ በጣም ከሚተማመኑባቸው ምርጥ መኮንኖች አንዱ ስለመሆናቸው በጦር መርከብ ላይ ነባር የሆነ ሠራዊት ሁሉ ያውቃቸዋል።
ኮማንደር ታመነ ጃለታ የተወለዱት በወለጋ ክፍለሃገር ሲሆን በኢትዮጵያ የሃገር መከላከያ ሠራዊት ውስጥ ማገልገል የጀመሩት እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ 1950ዎቹ በኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ ነበር፡ በተዋጊ አይሮፕላን አብራሪነት በመኮንነት ተመርቀው ከ 1,000 ሰአት በላይ በረዋል። በምን ምክንያት እንደሆነ ባይታወቅም ከኢትዮጵያ አየር ኃይል ከተሰናበቱ በኋላ እንደገና በኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ውስጥ በእጩ መኮንነት እንደ ኢትዮ አቆጣጠር በ1959 ዓም ለ 4 ዓመታት በኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ኮሌጅ በ NAVAL MARINE NAVIGATION EXCUTIVE OFFICER ሙያ ተምረው ከተመረቁ በኋላ ወያኔ መላውን የጦር ኃይል እስካፈረሰ ዘመን ድረስ ሃገራቸውን በቅንነት ፤ በጀግንነት፤ ያገለገሉ ምሁር ነበሩ።
ኮማንደር ታመነ ጃለታን የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ልዩ የሆነ ከባሕር ወደ መሬት ለምድር ጦሩ የመድፍ ድብደባ እና ባሕር ወለድ ኮማንዶ ጦር የማውረድ ድጋፍ አስፈላጊና ወሳኝ ጥያቄ ከምድር ጦር ዘመቻ መምሪያ ከመጣ እቅድና ዘአመራሩ የሚሰጠው ለርሳቸው ሲሰጥ እንደነበር የአደባባይ ምሥጢር ነበር።
-በአንድ ወቅት ያው እንደሚታወቀው የሻቢያ የኮማንዶ ጀልባአዛዥና ለወንብድና የሚያሰማራቸው ራሱ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ባልደረባ የነበረ ነውና፡ የተወሰኑ የሻቢያ ኮማንዶ ጀልባዎችን ምጽዋ ባሕር ኃይል መደብን እንዲደበድቡ እኩለ ሌሊት ላይ ይልካቸዋል። የሻቢያ ጀልባዎች ላይ የሚተክሏቸው የጦር መሳሪያዎች ባለ 14.5 ሚሊ ሜትር መትረየስና አሜሪካ ሥሪት Recoil የሌለው ( የማይራገጥ መድፍ) 106 ሚሊ ሜትር የቤኤም 21 ሮኬት መወንጨፊያውን ነጣጥለው ከ2 እስከ 3 ቧንቧ ( Barrel) አንድ ላይ በመግጠም በመኪና ባትሪ መወንጨፍ እንዲሁም በትከሻ የሚተኮስ ጸረ ታንክ ሮኬት ላውንቸር ብቻ ነው። እነዚህ የጦር መሣሪያዎች የጦር መርከብን የማስመጥ ኃይል የላቸውም። ምናልባት ተሳክቶላቸው የጦር መርከቡን ሞተር ክፍል ካልበሱ በስተቀር። ይህም ሆኖ ተሳክቶላቸው አያውቁም፡ በሬድዮ ፕሮፓጋንዳ ግን መላውን የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የጦር መርከበ እንዳሰመጡ ይለፈልፍልፉ እንደነበር አይረሳም።
ታዲያ ከእለታት አንድ ቀን ሻቢያ የባሕር ወንበዴ ጀልባዎችን መሬት ጥግ ጥግ እየቀዘፉ እንዲጓዙና ምጽዋ ባሕር ኃይል መደብን እንዲያጠቁ ይልካቸውና በወቅቱ የሰሜን ባሕር ኃይል እዝ ዘመቻ መምሪያ መኮንኑ ኮማንደር ታመነ ጃለታ ነበሩና ከእኩለ ሌሊት በኋላ ኢላማቸው ምን እንደሆን የማያውቁት ወንበዴዎች ተኩስ ከፈቱብን፡ በወቅቱ እራሴ የነበርኩት ፈጣን አጥቂ ጦር መርከብ FMB-162 ላይ ነበርና በወቅቱ ለሠራዊቱ ከወታደራዊ መረጃ በደረሰው መረጃ መሠረት FIRST DEGREES OF REDINESS ተእዛዝ መሠረት ለማንኛውም በማለት የጦር መርከቧ መኝታዬ ላይ ጫማዬን በማውለቅ ብቻ ነበር ጋደም ያልኩትና ከእኩለ ሌሊት በኋላ ላይ ዘብ ላይ የነበረ ብሔራዊ ወታደር መኝታ ክፍሌ ውስጥ መጥቶ ስሜን በመደጋገም ፒኦ ፍሬሠናይ ፤ እየተተኮሰብን ነው በማለት ጮኸ ፡ ጊዜ ሳላባክን ጫማዬን አድርጌ ወደ ውጭ መሪ ክፍል ስወጣ የመርከቧን MAST ላይ አንድ ጥይት ጭሮ አለፈ። የጦር መርከባችን ማሪን ኢንጂነሮች ጁኒየር ሌፍትናንት ጋሻው አበራ ፤ ፒኦ አበራ ነገዎ፤ ፒኦ መዝገበ እምብዛና ፒኦ ቦጋለ በየነ ፍጥነታቸው ለጉድ ነበርና 3ቱንም የመርከቧን ሞተር እንዳስነሱ ቶኪቻው የጦር መርከባችን አዛዥ ሌፍትናንት ጨዋቃ ሚደቅሳ በፍጥነት ከነበርንበት FSS Jetty ለቀን ስንወጣ፤ ፒኦ ፍሬሠናይ LOAD BOTH GUNMOUNTS, COMMENCE FIRE WHEN YOU SEE THE TARGET አለኝ። ምክንያቱም ከወደብ የምንወጣበት ግራና ቀኝ መሬት ነው ፤ ምናልባትም ከፊታችን ጀልባዎቹ ሊኖሩ ይችላሉ በማለት ነበር። የኛ ጦር መርከብ ሬዳር የራሽያ ስለሆነ በጥራት ለማሳየት ጊዜ ስለሚወስድበት ኮማንደር ታመነ ጃለታ ባሕር ላይ በቅኝት ለነበረችው P-204 አዛዥ ለሌፍትናንት ስለአባት ( TIGER) ባሕር ላይ የሚታዩትን ኢላማዎች POSITION ንገረኝ ባሉት መሠረት የ P-204 አዛዥ በፍጥነት ወደ ሰሜን አቅጣጫ እየሸሹ መሆናቸውን በሬድዮ ሲያስተላልፉ የኛ ጦር መርከብ ፍጥነት ስለነበራት በሬዳራችን ማየት እንደቻልን፡ ኮማንደር ታመነ ዓላማቸው ሁሉንም ወንበዴዎች በሕይወት ለመያዝ ነበርና ተከተሏቸው ብቻ ነበር እዝ የሚሰጡትና ለካስ ከኋላችን በፈጣን ጀልባዎች ማሪን ኮማንዶና ማሪን ዳይቨርስ ልከው ነበርና ወንበዴዎቹ ደግሞ የመረጡት ሽሽት ጀልባዎቹን መሬት አስነክተው ማምለጥ ነበርና እንደተገመተው ጀልባዎቹን AGROUND አድርገው ሲሰወሩ ለኛ ጦር መርከብ የመሳሪያችን ርቀት አካባቢውን መቆጣጠር ስለሚችል የ2 ኪሎ ሜትር ርቀት ኢላማ ስለተሰጠኝ ጥቂት ጥይት ለማሸበር ብቻ መሬቱ ላይ ተኮስኩ። ወዲያውኑ የኛ አንድ ጓድ ማሪን መሬቱ ላይ ወርደው አንዱ ብቻ እጅ አልሰጥም ብሎ ሲታኮስ ገድለው ሌሎቹን ማርከው እኛም 3 የሻቢያ ጀልባ ማርከን ጎትተን ምጽዋ ወደብ ገባን። በወቅቱ አንድ የኢትዮጵያ አየር ኃይል MI 24 ሄሊኮፕተር እግረኛ ወንበዴ ሊኖር ይችላል በማለት አካባቢውን ሲቃኝ ነበር፡፤
-- ሌላው ደግሞ ፡ ደቡብ የመን ከኢትዮጵያ ጋር የመረዳዳት የጦር ቃል ኪዳን ነበረንና በአንድ ወቅት በሶቪየት ራሽያኖች አቀነባባሪነት በመሪያቸው " በፕሬዚዳንት አሊ ናስር " ላይ መፈንቅለ መንግሥት ተደርጎ የጦር ኃይሉ ለ 2 ተከፍሎ እርስ በርስ ሲታኮስ የየመን ባሕር ኃይል ጦር መርከቦች ጥቂቶቹ እኛው ጋር አሰብ መጡ። ፕሬዚዳንት አሊ ናስርም አምልጠው አዲስ አበባ ገብተው ነበርና ከሃገር መከላከያ ሚንስትር ዋናው ግዳጅ የተሰጠው ለኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ነበር። ለግዳጅ የተዘጋጁት ጦር መርከቦች 1ኛ FRIGATE- 1617, LCT 1037 ባሕር ወለድ ኮማንዶ ጦር የጫነች ምድረነክ ጦር መርከብ፤LCT -1036 ታንኮችና ምድ ጦር ሠራዊት የጫነች ፤ FMB-160 እራሴው በ CHIEF GUNNER የነበርኩባት ነበር፡ የአጠቃላይ እዝ የተሰጠው ለኮማንደር ታመነ ጃለታ ነበር ፡ ጉዞው ተጀመረ፤ በወቅቱ የኢትዮጵያ መንግሥት ደቡብ የመን ላይ መፈንቅለ መንግሥት የተደረገው በሶቪየት ሩሲያኖች መሆኑን አላወቀም፡፤ ጉዞ ጀምረን ሳለ ዘመቻው ስም ባይኖረውም መርከበኛው ወዲያውኑ ነው " ዘመቻ ናስር " ማለት የጀመረው። ባበኤል ማንዳብ ከመድረሳችን አስቀድሞ የነበረው ማዕበል ለጉድ ነበርና ታንክ የጫነችው ምድረነክ ጦር መርከብ 1036 ከፊት ያለው RAMP በማእበሉ ሃይል ተገንጥሎ ወደቀ ። ውሃ ወደ ጦር መርከቧ ቢገባም የፈረንሣይ ሥሪትና አሰራሯ ምቹ ስለነበር ብዙ እግረኛ ሠራዊት ብትጭንም ያለምንም ጉዳት ነበርችና በአጋጣሚ የኢትዮጵያ መንግሥት በራሽያኖች አቀነባባሪነት መሆኑን ስለ መፈንቅለ መንግሥቱ ስለተረዳ ሁሉም የጦር መርከብ በአስቸኳይ ወደ አሰብ ወደብ ተመለሱ ተብሎ በሬድዮ መለእክት ተመለስን።
ኮማንደር ታመነ ጃለታ ምንጊዜም የማይረሱና ለወሳኝ የዘመቻ እቅዶች ቢጠሩም በተለያዩ የጦር መርከቦች ላይ በዋና አዛዥነት ሃገራቸውን ያገለገሉ ምርጥ መኮንን ነበሩ። ፎቶግራፋቸውን ባለማግኘቴ በአጋጣሚ የስፖርት ቱታ ለብሰው ከጦር መርከብ አባሎች ጋር የተነሱትን ፎቶግራፍ ነው የለጠፍኩት።
ክቡር ኮማንደር ታመነ ጃለታ በአደረባቸው ሕመም ምክንያት እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ 1985 ዓም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተውናል። እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን።