የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ኃይል ታጥቋቸው ከነበሩት የጦር መርከቦች የፈጣን ተዋጊ 201ኛ ስኳድሮን ዘመናዊ የጦር መርከቦች በቀይ ባሕራችን ላይ ዝነኛ የነበሩ የዩኤስ አሜሪካን ስሪት የነበሩ ናቸው። የጦር መርከቦቹ ግዢ ወይም ዕቅድ የተከናወነው በዘመነ አጼ ኃይለሥላሤ እነደነበርና ኢትዮጵያ ከፊውዳላዊ ሥርአት ወደ ሶሻሊዝም ከ1966 አብዮት በኋላ ከአሜሪካን ጋር ያላትን ግንኙነት በማቋረጧ፡ ዩኤስ አሜሪካን ከአጼ ኃይለሥላሴ ጋር የነበረውን አጠቃላይ የጦር መሣሪያ ውል በማፍረሷ ምክንያት ለደርግ የኢትዮጵያ መንግሥት የጦር መሣሪያ ማዕቀብ በማድረጓ ምክንያት፡ አራቱን ብቻ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1969ዓም አስረክባለች። ሆኖም ታዲያ በአራቱም የጦር መርከቦች ላይ ዋናው የጦር መሣሪያ EMERLEK 30mm GUNMOUNT በአንዷ ላይ ብቻ ማለትም P-202 ላይ ብቻ ተተክሎና እንዲሁም በአራቱም የጦር መርከቦች የውጭ መሪ ክፍል ላይ ግራና ቀኝ አንድ አንድ ባለ50 ካሊበር መትረየስና አንድ ባለ 81 ሚሜትር ባለቃታ ሞርታር ብቻ በመትከል ለኢትዮጵያ ባሕር ኃይል እንዲረከብ ተደርጓል።
የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ኦርድናንስ መኮንኖች ሁኔታውን አጥንተው ሶቪየት ሠራሽ ዙ-23 የሚባል ባለሁለት አፈሙዝ ቀላል አውቶማቲክ ፀረ አውሮፕላን መድፍ እንዲተከል አድርገው፡ በቀይ ባሕር ላይ ሻቢያ ያሰማራቸውን ወንበዴዎች የባሕር ኃይላችን ጀግኖች መርከበኞች እያሳደዱ ሲቀጡባቸው የነበሩ ዝነኛ የጦር መርከቦቻችን ነበሩ። ሻቢያ በረሃ ላይ በተከለው የሬድዮ ጣቢያ ሁሉንም አስምጠናል በማለት ፕሮፓጋንዳ ሲነዙ፡ በወቅቱ የነበረው የደርግ መንግሥት ሁኔታውን እኛ መንግሥት ስለሆንን ማስተባበል አያስፈልገንም በማለት፡ ሕዝባችንንም ሆነ ለሌላው የጦር ኃይሎች ክፍል እውነት እንዲመስል የተደረገ ስህተት ነበር። ሻቢያዎች አስምጠናል ያሏቸውን የጦር መርከቦቻችን እዙህ ፎቶግራፍዋ የምትታየዋን P-201, P-203, P-204 እና በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያውን የረጅም ርቀት ሚሳይል ተሞክሮ የተሳካልንን፡ ሚሳይል ወንጫፊ የጦር መርከባችንን FMB-163ን ጨምሮ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1989 ዓም ፡ የወያኔው ጠ/ ሚንስትር መለስ ዜናው ለሻቢያ አስረክቧል። የሻቢያ ጀልባዎች ጦር መሣሪያ እንኳንስ መርከብን የሚያህል ነገር ሊያሰመጥ ቀርቶ ተራ ጀልባ እንኳን የማይጎዳ በፕሮፓጋንዳ ብቻ የተቀነባበረ አዋጅና ቀልድ ነበር። እርግጥ ነው ከየደሴቱ ሥር ተደብቀው አደጋ ለመፍጠር ተፍጨርጭረው ከ15 ጀልባ ወደመጣበት ሲመለስ የነበረው 5 ወይም 4 ብቻ ነበር። ሌላውን መድፈኞቻችን አነጣጥረው በመተኮስ የቀይ ባሕር ሻርክ ምሳና እራት በማድረግ የሻቢያን ወንበዴዎች ዋጋቸውን ሰጥተዋቸዋል።
201ኛው ፈጣን ተዋጊ ስኳድሮን የጦር መርከቦቻችን ሥሪታቸው አሜሪካን ሃገር ቢሆንም በውስጣቸው የተተከሉት የቴክኒክ ዕቃዎች፡ ENGINE ወይም ሞተራቸው MTU በዚያን ጊዜ ምዕራብ ጀርመን፤ ሬዳር DECCA እንግሊዝ እንደነበር በመርከቦቹ ላይ የነበረው የስኳድሮኑ መጽሄት ላይ ተብራርቶ እንደነበርና በተለማማጅነት በኢትዮጵያ ባሕር ኃይላችን ለመጀመሪያ ጊዜ ያገለገልኩባት የጦር መርከባችን P-201 ትዝታዋ ምንጊዜም አይጠፋም።