| የባሕር ጠለቅ ኮማንዶ ስለ ባሕር ጠለቅ ኮማንዶ የጦርነት ግዳጅ ሙያዬ ባይሆንም ከከፍተኛ የባሕር ኃይል መኮንን መምሕራኖቼ ከተረዳሁትና ራሴም ካየኋቸው፦ የባሕር ጠለቅ ኮማንዶ ስልጠና ዋናውን ወሳኝ የባሕርም ይሁን በባሕር ጠረፍ አካባቢ ወሳኝና በጥንቃቄ የተሰላ ግዳጅ ይወጡ ዘንድ ማንም ወታደር ተሰጥቶት የማያውቀውን ኃላፊነት ወስደው ለዋናው ተዋጊ፡ ለጦር መርከቦችም ይሁን ለባሕር ወለድ ጦር ማሪን ኮማንዶ የውጊያ አመቻች አብሪ እንደመሆናቸው መጠን በአእምሮ አስተሳሰብና በሰውነት ጠንካራ እንዲሆኑ ስልጠናው በጣም በጣም ከባድ ነው። ከጣሊያንኛው ቃል Uomorana ከሚለውና በጠለቃ ወቅት ከሚለብሱት ልዩ ጠንካራ TIGHT ልብስና የቀዘፋው ጫማቸው የተነሳ ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ FROGMEN ተብሏል። በሲቪሉ የ DIVING CLUB ስፖርት ማሕበርም SCUBA DIVING ትእብሎም ይጠራሉ። በአሜሪካን ባሕር ኃይልም NAVY SEALS በመባልም ይጠራሉ። - የባሕር ጠለቅ ኮማንዶ ስልጠና በባሕር ውስጥ እጃቸው ላይ እንደ ሰአት ባሠሩት የማግኔቲክ ኮምፓስ የረጅም ርቀት የባሕር ውስጥ ለውስጥ ዋና በምጓዝ ጠላት ያጠመደውን የባሕር ውስጥ ፈንጂ ( MOORED MINE) ማምከን - የጠላት የጦር መርከብ የሚመጣበትን አቅጣጫ ( COURSE) ተነግሯቸው የባሕር ውስጥ ፈንጂ የማጥመድ ግዳጅ ይወጣሉ። - ልክ እንደ አየር ወለድ ከአይሮፕላን ዘለው ባሕር ውስጥ በመግባት የተሰጣቸውን ሚሽን ይወጣሉ። - የባሕር ወለድ ማሪን ኮማንዶ ጦር በምድረነክ የጦር መርከብ ወደ መሬት ሠራዊት ለማውረድ ከመጠጋቱ አስቀድሞ በባሕር ውስጥ ለውስጥ ተጉዘው የባሕር ጥልቀቱን የሚለኩና በአካባቢው ስላለው የጥልቀት ውስጥ መረጃ ድንጋያማ፤አሸዋማ ወይም ቦታው አመቺ መሆኑንና አለመሆኑን መረጃ ይሰበስባሉ። - የጠላት ሃገር ወደብ አካባቢ ከፈጣን ጀልባቸው ዘለው ውስጥ ለውስጥ ተጉዘው በጠላት የጦር መርከብም ይሁን በወደብ አካባቢ ባለው ወታደራዊ ዒላማ ላይ ፈንጂ በማጥመድ ጥቃት ያደርጋሉ። ስለጠናው በጣም ከባድ ከመሆኑ የተነሳ የደቡብ የመን ባሕር ኃይል የላካቸው 20 የሚሆኑ ሰልጣኞች ውስጥ ስልጠናውን ያጠናቀቁት 2 አባሎች ብቻ እንደነበሩ አይረሳኝም። - ሌላው የደቡብ ሱዳን ነሳ አውጪ ጦር ከሰሚን ሱዳን ጋር በውጊያ ሳሉ ከታጋዮቹ መሃል ተመርጠው ምጽዋ ባሕር መደብ በኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ባሕር ጠለቅ ኮማንዶ ሰልጥነው ኮርሱን ጨርሰው ወደ ሃገራቸው በተመለሱ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ሱዳን ወደብ ላይ በባህር ውስጥ ተጉዘው 2 የሱዳን ባሕር ኃይል የጦር መርከብ ማፈንዳታቸውን በጀርመን ሬድዮ የአማርኛ ፕሮግራም ማዳመጣችንን አይረሳኝም። ውድ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የባሕር ጠለቅ ኮማንዶ አባላት፡ ስለ ሃገራችን ኢትዮጵያ ላደረጋችሁት ውለታ የኢትዮጵያ አምላክ እድሜና ጤና ይስጣጭሁ። በግዳጅ ላይ ለተሰዉት መላው የኢትዮጵያ ወታደሮች ሁሉ፡ አምላክ ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን። |