| ክቡር ኮማንደር ዘለቀ ቦጋለ በኢትዮጵያ ሃገራችን ስማቸው በታላቅ ትሩፋት ከሚነሱ የኢትዮጵትያ ባሕር ኃይል ካፈራቸው የሃገራችን ባለውለታዎች አንዱ ታላቅ ክቡር ሰው ነበሩ። በውትድርናውም ሆነ በሲቪሉ ዓለም ሕይወታቸውን በሙሉ ከራሳቸው ይልቅ ለእናት ዓለም ኢትዮጵያ የተግባር ባለውለታ ክቡር ከፍተኛ መኮንን ነበሩ። ኮማንደር ዘለቀ ቦጋለ መስከረም 22 ቀን 1934 ዓም በሓረር ከተማ ተወለዱ። አባታቸው አቶ ቦጋለ ጃቶ ነጋዴና እንዲሁም ኢትዮጵያ ሃገራችን በፋሽስት ኢጣሊያ ወታደሮች ስትወረር በአርበኝነት ስለሃገራቸው እናት ኢትዮጵያ ፍቅር ዘምተዋል። አባታቸው አቶ ቦጋለ ጃቶ ልጆቻቸውን በኢትዮጵያዊነት ሥነምግባር ማሳደጋቸውና ክቡር ኮማንደር ዘለቀ ቦጋለም 5ኛና የመጨረሻ ልጃቸው እንደሆኑ በውጭ ሃገር ያሉ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች አብራርተው እንደነበር አይዘነጋም። ኮማንደር ዘለቀ ቦጋለ የከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት ሓረር ከተማ ባለው፡ ራስ መኮንን ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው። የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ሲመሠረት እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ 1948 ዓም የመጀመሪያው እጩ መኮንኖች ከነበሩት አንዱ ነበሩ። በኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ኮሌጅ አካዳሚ በነበሩ ወቅት ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ የተለያዩ ሽልማቶችን ተቀብለዋል። ኮማንደር ዘለቀ ቦጋለ በኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ታሪክ የመጀመሪያው የጦር መርከብ ካፒቴን ( THE FIRST ETHIOPIAN NAVAL OFFICER TO COMMAND THE FLAG SHIP OF THE NAVY) ሲሆኑ የጦር መርከቧም HMS ( ታላቋ ጦር መርከብ ኢትዮጵያ ) ነበረች። ከዚያም በኋላም የአጠቃላይ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ሆነውም አገልግለዋል። በዘመነ የደርግ ኢትዮጵያ መንግሥት ኮማንደር ዘለቀ " አጠቃላይ የባሕር ትርናስፖርት ሥራ አስኪያጅ በመሆን ለ 17 ዓመታት አገልግለዋል።" የሁለቱም የምጽዋና አሰብ ወደብና እንዲሁም በሃገር ውስጥ ያሉትን የጣና ጎርጎራ፤ ሻላ ፤ አቢያታና አርባ ምንጭ ያሉትን ሁሉ ዘመናዊ እንዲሆኑ ደከመኝ ሰለቸኝ፡ሳይሉ የቱሪስት መስህብ እንዲሆኑና በተለይም የአሰብ ወደብ በዓለም አቀፍ እኩሌታ አገልግሎት እንዲኖረው ግዙፍ ክሬኖችና ለሠራተኞችም የመኖሪያ ቤቶችንና ልዩ የሆነ ክበብ በማሰራት የወደብ አገልግሎቱን ፈጣን ይዘት እንዲኖረው በሚያስደንቅ ሁኔታ ለውጠው እንደነበር አይዘነጋም። እያንዳንዱ ሠራተኛ ኃላፊነቱን በተግባር ይወጣ ዘንድ የቅርብ ክትትል በማድረግ ይሰነፈውን በመገሰጽ፤ ጎበዙን በማበረታታት ሃገራችን ኢትዮጵያን ታላቅ ደረጃ አድርሰዋት ነበር። ኮማንደር ዘለቀ ቦጋለ ከኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ኮሌጅ አካዳሚ ተመርቀው ከወጡ በኋላ የተማሩት፦ በ USA አሜሪካን ሃገር SAN DIEGO NAVAL ACADEMY እና በእንግሊዝ ሃገር BRITISH NAVAL ACADEMY IN DARTMOUTH የተማሩትም ሙያ NAVAL WARFARE AND EXCUTIVE / LEADERSHIP , ከዚያም በ BIRMINGHAM UNIVERSITY POST GRADUATE በ DIPLOMA IN THE SOCIAL SCIENCE AND ARTS.ነው። ክቡር ኮማንደር ዘለቀ ቦጋለ ስለሃገራቸውና ወገናቸው ውለታና የማያሰልስ የአስተዳደራዊ ብቃታቸውና ጥረታቸው ፤ ስለወደቦቹ ዘመናዊነት ፍጥነት ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያም በአንድ ወቅት ሲናገሩ "" ኢትዮጵያ የኮማንደር ዘለቀ ቦጋለ ተመሳሳይ የተግባር ሥራ አስኪያጅ ቢኖራት የተ በደረሰች ነበር "" በማለት አድናቆታቸውንና ምሥጋናቸውን ተናግረው እንደነበር በቅርብ የሰሙ ምክትሎቻቸው ሲናገሩም ሰምተናል። ክቡር ኮማንደር ዘለቀ ቦጋለ እንደ አውሮፓ አቆጣተር JUNE 8 2009 እኩለ ቀን ላይ አርፈዋል። ክቡር ኮማንደር ዘለቀ የ 2 ልጆች አባት ማለትም አሁን የአርበኞች ግንቦት 7 የውጭ፡ጉዳይ ኃላፊው የክቡር አቶ ነዓምን ዘለቀ እና የአቶ አድነው ዘለቀ እንዲሁም የልጅ ልጆቻቸው እምአእላፍ ነአምን እና ኢዮር ነዓምን አባት ነበሩ። የኢትዮጵያ አምላክ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማርልን። አሜን። |
ክቡር ኮማንደር ዘለቀ ቦጋለ ማናቸው? እያንዱን ፎቶግራፍ ለማየት ፎቶውን ይጫኑ ( Click here to comment & read comments)28/11/2015
0 Comments
Your comment will be posted after it is approved.
Leave a Reply. |