የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ማሪን ኮማንዶ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1958 ዓም ተቋቋመ። የመጀመሪያዎቹ የማሪን ኮማንዶ አባላት በእሥራኤል ሃገር እና ከዚያም በብሪታኒያ ሮያል ማሪን ኮማንዶ አሠልጣኞች ሰልጥነው ከተመለሱ በኋላ የባሕር ኃይሉ የራሱን የማሪን ኮማንዶ ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት በኤርትራ እምባቲካላ በሚባለው ቦታ መሠረተ። ሥልጠናው ሲመሠረት ዋና አዛዥ ሆነው የተሾሙት ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ የእሥራኤል ማሪን ኮማንዶ የግሪን ቤሬት ማሰልጠኛ ምሩቅ ስለነበሩ የማሪን ኮማንዶ አዛዥ ሆነው ተሾሙ።
ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ ወደ እሥራኤል ሃገር ለማሪን ኮማንዶ ከመላካቸው በፊት በሓረር ጦር አካዳሚ በመጀመሪያ የ 4 ዓመት የአካዳሚክስና የወታደራዊ ሳይንስ ተምረው ፤ በአሜሪካን ሃገር በታወቀ ዩኒቨርስቲ የሕግ ትምህርትና እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በማእረግ የተመረቁ ምሁር ናቸው።
የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ማሪን ኮማንዶ አባላት በወታደራዊ ግዳጅ ዘመቻ በቀይ ባሕር ደሴቶች ላይ በማድፈጥ በተለያዩ ጊዜያት ያለምንም ተኩስ በኮማንዶ ታክቲክ ብቻ ሻቢያ የጦር መሳሪያና ትጥቅ ለማመላለስ ወንበዴዎቹ ከየአረብ ሃገራት ሲመላለሱ የሚደበቁበት ደሴት ላይ በማድፈጥ ከነሕይወታቸው በመያዝ ተደጋጋሚ አኩሪ ገድል ፈጽመዋል።
የማሪን ኮማንዶ አባላት ግዳጃቸው በባሕር ወለድ LCM ( Landing Craft Marin) ጀልባዎች መሬት ላይ በመውረድ የሻቢያ ደፈጣ ተዋጊዎችን የሚማረከውን ማርከው ተኩስ የከፈተባቸውን ገድለውና፤ ተሰውተው ስለ ኢትዮጵያ ሃገራችን አንድነት በሚገባ ተዋድቀዋል። በተለይም እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ 1969ዓም የሶማሊያ ግዙፍ ሠራዊት ሃገራችን ኢትዮጵያን በሓረርጌ እና በባሌ ክፍለሃገራት 750 ኪሎ ሜትር በወረራ በያዘብን ወቅት፡ የማሪን ኮማንዶ መኮንኖች የፓራ ኮማንዶና የሚሊሺያው ሠራዊትን በማዝመት ታላቅ ገድል የፈጸሙ ውድ ኢትዮጵያውያን ናቸው።
በምሥራቅ ጦር ግምባር ከዘመቱት ጥቂቶቹ ፦ ሌ/ኮማንደር መሰለ ደሥታ ፤ ሌ/ኮማንደር ተስፋዬ ውዴ፤ ሌ/ኮማንደር ፋንቱ፤ ሌፍትናንት መኩሪያ ዲዲማ፤ ሌ/ኮማንደር አለማየሁ ጆቴ እና ሌፍትናንት ዋቅጋሪ አሞሳ እንዲሁም ሌሎችም ስማቸውን የማላስታውሳቸው የባሕር ኃይል አባላት ናቸው።
የአየር ወለድ ክፍለጦር ከ1969 እስከ 1970ዓም ሲፈርስ የማሪን ኮማንዶ ክፍልም ፈርሶ እንደገና እነደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1973 ዓም አየርወለድ ሲመሠረት የማሪን ኮማንዶ ክፍልም ተቋቁሞ፡ በአየርወለድ የኮማንዶ ስልጠና ከተሰጣቸው በኋላ በሰሜን ኮሪያ የቴኳንዶ ወታደራዊ አሠልጣኞች ሠልጥነው፡ እንደቀድሞዎቹ ማሪኖች አዲሶቹም በተለያዩ የቀይ ባሕር ደሴቶች ላይ በማድፈጥ የሻቢያን ስንቅና ትጥቅ በመማረክና፡ የጦር መርከቦች የባህር ወንበዴዎችን አባረው ለመምታት ሲከታተሉ ጀልባቸውን ጥለው ወደ መሬት አስነክተው የፈረጠጡትን የሻቢያ ወንብዴዎችን በከባሕር ጠለቅ ኮማንዶ ጋር በመተባበር በ ZODIAC ጀልባ መሬት ላይ ወርደው ከነሕይወታቸው ማርከዋል።
የማሪን ኮማንዶ አባላት በዚህ ብቻ ሳይወሰኑ፡ ቀደም ብሎ በ SPECIAL FORCE ኮማንዶ የሰለጠኑት የማሪን ኮማንዶ አባላት ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ ሃብተማርያም፡ በሚመሩት የአይሮፕላን ጠለፋ እንዳይደረግ በ ANTI HIJACKER የስውር ጥበቃ በማድረግ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አንድም ጊዜ አይሮፕላኖቻችን እንዳይጠለፉ ታላቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል።
ሳይጻፍ ቀረ የምትሉት ካለ የማሪን ኮማንዶ አባላት በ Facebook አካውንቴ በ Message በኩል ብትልኩልኝ EDIT በማድረግ አስተካከለዋለሁ
በግዳጅ ላይ ስለሃገራችን አንድነት የተሰዉትን አምላክ እግዚአብሔር ነፍስ ይማርልን፤ በሕይወት ያሉትንም እድሜ ይስጥልን
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!