የኢትዮጵያ ሃገር መከላከያ ሠራዊት ተቋምን እና የክልል ኃይል ሥለሚባለው ቁልፍ ጉዳይ፡ ለጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አሕመድ የምለው ጉዳይ አለኝ። ይህ አመለካከቴ የአብዛኛው የቀድሞው ሠራዊት አባላትና የሃገራችን ጉዳይ በከፍተኛ ደረጃ ከሚያሣስባቸው ኢትዮጵያውያን ጋር የሚጋራ ሃገራዊ ኃላፊነት የሚሰማቸው ከዘር ፖለቲካ በፀዱ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሚንፀባረቅ በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው።
የሃገራችን የመከላከያ ሠራዊት ብቃት ከፍተኛ ነው እያሉ የሚናገሩትን የባሕላዊ ሹመት ላይ ባሉት የሠራዊቱ አመራሮች የሚናገሩትን ቃለ ምልልስ ማመን በጣም ይከብዳል፤ በበኩሌ ለመቀበል በጣም ይከብደኛል። አሁን ያለው የሃገር መከላከያ ሠራዊት የተተካው ቀደም ብሎ በደፈጣ ውጊያ ሃገር ሲያሸብሩት በነበሩት የሕወሃት የጫካ ወንበዴዎች አማካኝነት መሆኑ የአደባባይ ምሥጢር ነው። ከኤርትራ ጋር የሠላም ጎዳና ላይ ብንሆንም የእነዚህን ሽፍቶች ወታደራዊ ብቃት ለመገምገም የባድመ ጦርነትን ማስታወስ ግድ ይላል። እነ ስዬ አብርሃና ፃድቃን ገ/ተንሣይ የሚመሩት ጦር አብሯቸው ጫካ የነበረና ከላይ ከአመራሮቹ ከነፃድቃንና ስዬ አብርሃ ጀምሮ የደፈጣ ተዋጊና ምንም ሚሊታሪ ሳይንስ የማያውቁ የጫካ ቃፊሮች ከመሆናቸውም በላይ ሻቢያ ባድመን አልፎ እስከ ሽራሮ ድረስ ወረራ አድርጎ የሚመሩትን ታንክና ሠራዊት ድራሹን አጥፍቶ ሲወቅጣቸው የመከላከያ ሠራዊት ኤታ ሜጀር ሹም የተባለው ፃድቃን ገ/ተንሣይ እንደ እቃ አታስፈልጉም እኛ ጀግኖች ነን በማለት የጣሉዋቸውን የቀድሞውን ሠራዊት አባላት እባካችሁ ተወረርን ኧረ ድረሱልን ብለው አለቃቅሰው ለቀድሞው ሠራዊት ጥሪ ሲያደርጉ ፡ ከሠራዊቱ አባላት ከፍተኛ መኮንኖች " የሕብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግናው አየርወለድ ክቡር ጄኔራል ተስፋዬ ኃ/ማ ፤ ከምድርጦር ክቡር ጄኔራል በኃይሉ ክንዴ ፤ ከአየር ኃይል የቀድሞው የአየር ኃይል ዘመቻ መኮንኑ ክቡር ጄኔራል ተጫኔ መስፍንና ሌሎችም በ 10,000 የሚቆጠሩ የቀድሞው ጦር አባላት ከታንከኛ ከመድፈኛና እግረኛ ተውጣጥተው አለን ለሃገራችን ኢትዮጵያ ብለው ሲደራጁም በመሃላቸው የወያኔ ንክኪ በጥባጭ እንዳይኖር ፃድቃንን አስጠንቅቀው ለአጭር ጊዜ አዲስ የተመለመሉ ወጣቶችን አሠልጥነው፤ እንዲሁም ምርጥ የአየር ኃይላችን የቀድሞው አብራሪዎችና ቴክኒሺያኖች በስደት ኡጋንዳ ፤ ጂቡቲና ኬንያ የነበሩት ጥሪ ሲደረግላቸው ምንም ሳያቅማሙ በቀላሉ ሻቢያን ማስተንፈስ እንደሚችሉ አውቀው ዘመቱ።
ያ ዘመቻ ለቀድሞው ጦር ቀላል ነበር ፤ ምክንያቱም በደርግ የኢትዮጵያ መንግሥት ዘመን ሲዋጉ የነበረው ከአንድ አመፀኛ ወንበዴ ጋር ሳይሆን ከሶማሊያ ወራሪ ጦር ጋር በምሥራቅ ኢትዮጵያ ፤ በሰሜን ኤርትራ ውስጥና ትግራይ ውስጥ ከሻቢያ ፤ ጀብሃ ፤ አልዋህዳና ከወያኔ ጋር ፤ በወለጋ ከሱዳን ጦርና ከኦነግ ደፈጣ ወንበዴዎች ጋር ፤ በጎንደር ከኢዲዩ ጋር በመሃል ሃገር ከኢህአፓ ጋር....ወዘተርፈ ነበርና ይህ ጦርነት ለቀድሞው ሠራዊት ተኩስ አቁም ተብሎ የተፈረደበትን ቂም ለመወጣት ክንዱን ሻቢያ ላይ አሳይቶ በ 2 ቀናት ውስጥ ጦርነቱ ኤርትራ ውስጥ ነበር። የአየር ሃይላችን አባላት ለሁለት ዓመታት የተለዩዋቸውን ተዋጊ አይሮፕላኖች በጄኔራል ተጫነ መስፍን አመራር Refreshment Course አድርገው ተለማምደው ማንነታቸውን ማሳየታቸው አይዘነጋንም ወያኔ ታሪካቸውን ቢቀብረውም።
ወያኔዎች ሚዲያውን በሙሉ በራሳቸው ሥር ስላደረጉት የጄኔራል ተስፋዬ ኃ/ማርያምን አመራር ለወያኔ ሳሞራ የኑስ ፤ የጄኔራል በኃይሉ ክንዴን አመራር ለወያኔ ፃድቃን ገ/ተንሣይ ፤ የጄኔራል ተጫኔ መስፍንን አመራር ለወያኔ አበበ ተ/ኃይማኖት በማድረግ ድሉም አመራሩም የነርሱ እንደሆነ አድርገው ፕሮፓጋንዳ ነዙበት። በዛላንበሳ በኩል ሲመሩ የነበሩት ክቡር ጄኔራል ተሳፋዬ ኃ/ማ ሻቢያን ለማደናበር በሰው ቅርፅ የተሰራ አሻንጉሊት ውስጥ ፈንጂ እንዲደረግ አድርገው ሻቢያ ጦር መሃል እንዲወድቅ በፓራሹት እንዲወርድ ያደረጉበት ብልህ አመራር ውጤት ሻቢያዎች አየወለዶችን ከነሕይወት እንማርክ ብለው ፓራሹት ወራጆችን ተከትለው ያለቁበትን ታክቲክ ከባድ የነበረውን ዘመቻ በቀላሉ አሸንፈው ሠራዊቱ እስከ ሰንአፌ ድረስ ድል ማስገንዘቡን እናስታውሳለን፤ እርሳቸው ከኢሳት ሚዲያ ጋር በጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና የተደረገላቸው ቃለ ምልልስ ላይም ዘግበውታል። ያ የባድመ የድሉ ዋነኛው ባለቤት የቀድሞው ጦር 10ኛ ክፍለጦር በሚል ተደራጅቶ ወያኔን ከውርደት ያዳነው ጦር በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ እንደገና ተበተነ። ዝርዝር ሁኔታውን ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ተገልጿል ፤ ዩትዩብ ላይ ታገኙታላችሁ።
ከላይ የዘረዘርኩት እውነታን ለወቅቱ መሪያችን ለጠቅላይ ሚንስትር አቢይና እርሱ ለሚመራቸው ለሲቪልና ለወታደራዊ አመራር ባለሥልጣኖች ማስታወሻ ምሳሌ እንዲሆን እንጂ አሁንም ከኤርትራ ጋር ጦርነት እናድርግ በሚል እሳቤ ምክንያት አይደለም ይህንን ማስታወሻ የፃፍኩትና፡ ጠ/ሚ አቢይ ይህንን ጉዳይ በጥልቀት አስቦ የታላላቅ ሃገራት መሪዎች እንኳን እነ አሜሪካና ሩሲያ አውሮፓ ታላላቅ ሃገራት መሪዎች ሥልጣን ሲረከቡ ዋና የደህንነትና የመከላከያ ሠራዊታቸውን የሚያማክሩት በአገልግሎት ላይ ያሉትን ከፍተኛ መኳንንትን ሳይሆን በልምድና ኣመራር ለረጅም ዘመናት በወታደራዊ አገልግሎት ዝና ያላቸውን ጡረታ ላይ ያሉትን ፊልድ ማርሻሎችን ፤ ጄኔራሎችን የቅርብ አማካሪዎች በማድረግ የሃገራቸውን ደህንነትና የመከላከያ ሠራዊታቸውን ብቃት ይገነባሉ።
እነሆ ታዲያ ለጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አሕመድ የማመለክተው ጉዳይ የምታዘውን የመከላከያ ሠራዊት አዛዦች ሪፖርት ብቻ በመቀበል አትዘናጋ ? በቀድሞው ሠራዊት ልምድ ባላቸው ጄኔራሎች የመከላከያው ሠራዊቱን ብቃት ምን ያህል ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል አስገምግም ? ክቡር አየርወለድ ጄኔራል ተስፋዬ ኃ/ማ ፤ ክቡር የታንከኛና የሜካናይዝድ ተዋጊ ጦር ውጤታማው ጀግናው ጄኔራል ካሣዬ ጨመዳ ፤ በምሥራቁ ጦር ግምባር የወራሪውን የሶማሊያን ጦር በቦምብ ጣይ ጄት ተዋጊ አይሮፕላን በማብረር ዳይቭ እየገቡ ካደባዩት ምርጥ የአየር ኃይላችን አብራሪውን ጄኔራል ተጫኔ መስፍንን ወታደራዊ ሳይንስ እውቀታቸውን እንዲያካፍሉ እባክህ በአማካሪነትና መሠረታዊ እውቀታቸውንና ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ አቅርባቸው ፤ መልካም ጥሪም አድርግላቸው።
ፍሬሠናይ ከበደ